ባህር ዳር ከነማ ኢትዮጵያ መድህንን አሸነፈ።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 10:00 ሰዓት በተካሄደዉ ጨዋታ ባህር ዳር ከነማ ኢትዮጵያ መድህንን 3 ለ 2 አሸነፈ። የባህርዳር ከነማን 3 የማሸነፊያ ጎሎች ተስፋየ ታምራት በ38ኛዉ ፉአድ ፈረጃ በ52ኛዉ ሀብታሙ ታደሰ በ64ኛዉ ደቂቃ አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ መድህንን ሁለት ጎሎች ብሩክ ሙሉጌታ በ35ኛዉ ኪቲካ ጅማ በ94ኛዉ ደቂቃ አስቆጥረዋል። በቀጣዩ 7ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር ኢትዮጵያ መድህን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ አርብ ህዳር 2 10:00 ሰዓት የሚጫወቱ ሲሆን ባህርዳር ከነማ ከአርባምንጭ ከተማ ቅዳሜ ህዳር 3 10:00 ሰዓት ላይ ይጫወታል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.