ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ሰዓት ላይ ማስተካከያ አደረገ።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ሰዓት ላይ ማስተካከያ አደረገ።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከቀናት እረፍት በኋላ በድሬዳዋ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀምራል።
ከዚህ ቀደም በወጣዉ የጨዋታ ሰዓት ላይ ማስተካከያ ተደርጓል።
ኢትዮጵያ መድህን ከባህርዳር ከነማ 10:00 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
ኢትዮጵያ መድህን በሊጉ 12 ነጥቦችን በመሰብሰብ በቅዱስ ጊዮርጊስ በግብ ክፍያ ተበልጦ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ባህርዳር ከነማ 8 ነጥብ በመሰብሰብ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና 1:00 ሰዓት ላይ ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ።
ድሬዳዋ ከተማ በ4 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በ10 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

