አርጀቲና ሜክሲኮን አሸነፈች
አርጀቲና ሜክሲኮን አሸነፈች
የኳታር 2022 የፊፋ የአለም ዋንጫ የምድብ 3 ሁለተኛ ዙር ጨዋታ ቅዳሜ ህዳር 17 ቀን 2015
ምሽት 4 ሰአት በተደረገ ጨዋታ
አርጀቲና ሜክሲኮን በሜሲና በፈርናንዴዝ ጎሎች 2ለ0 አሸነፈች።
አርጀንቲና 2-0 ሜክሲኮ
⚽️ሜሲ 64′
⚽️ፈርናንዴዝ 84′
በምድቡ መጀመሪያ ጨዋታ ሳውዲ አረቢያ አርጀንቲናን 2 ለ 1 ስታሸንፍ ፖላንድና ሜክሲኮ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል ።
ዛሬ ቀን 10 ሰአት ላይ ደግሞ በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ፖላንድ ሳውድአረቢያን 2 ለ0 አሸንፋለች
በዚህ መሠረት
👉ፖላንድ በ4 ነጥብና 2 ንጹህ ጎል አንደኛ
👉አርጀንቲና በ3 ነጥብና በ1 ንጹህ ጎል ሁለተኛ ።
👉ሳውዲ አረብያ በ3 ነጥብና በ1 የግብ እዳ ሶስተኛ
👉ሜክሲኮን በ1 ነጥብ በ2 የግብ እዳ አራተኛ ላይ ተቀምጠዋል።
በቀጣይ የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ህዳር 21 ቀን 2015 አ/ም
👉 ፖላንድ ከአርጀንቲና
👉ሳውድአረቢያ ከሜክሲኮ የሚጋጠሙ ይሆናል ።
👉በዛሬው ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ ስምንት ማድረስ ችሏል በዚች ጎል ምክኒያት የዲያጎ ማራዶናን የ8 ጎል ታሪክ ተጋርቷል።

