የአርሴናል ተጫዋች ፈላጊው በዝቷል

እንግሊዛዊው የመስመር ተጫዋች ኤንስሊ ሜትላንድ ኒልስ የዝውውር መስኮቱ የፊታችን ሰኞ ከመጠናቀቁ በፊት ወደ ሌላ ክለብ በውሰት ለማቅናት ተቃርቧል ።
• ዌስትብሮም የተጫዋቹ ፈላጊ ሆነው ቢቀርቡም በዛሬው ዕለት ሳውዝሀምፕተን ሌላኛቸው የተጫዋቹ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል ።
• ከሁለቱ ክለቦች በተጫማሪም በትላንትናው ዕለት በወጣ መረጃ በደረጃ ሰንጠረዡ አራት ውስጥ ይገኙ በነበሩ ቡድኖች መካከል የ ሜትላንድ ኒልስ ፈላጊዎች መኖራቸው ተገልጿል ።
• ሳውዝሀምፕተን በትላንትናው ዕለት አመሻሹ ላይ ከ አርሴናል ሀላፊዎች ጋር መነጋገራቸው ሲገለፅ እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ለማስፈረም ጥያቄ አቅርበዋል ።
• የአርሴናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ሜትላንድ ኒልስ ከ ዌስትብሮም ይልቅ ሳውዝሀምፕተን እንዲገባ መፈለጋቸው ተነግሯል ።
• ሜትላንድ ኒልስ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በፕርሚየር ሊጉ አምስት ጨዋታዎችን ብቻ በቋሚ አሰላለፍ ጀምሮ መጫወት ችሏል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.