ማንችስተር ዩናይትድ ከ ተጫዋቻቸው ጋር ለመለያየት ተቃርበዋል
ቀያይ ሴጣኖቹ ከ 30 ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቻቸው ማርኮስ ሮሆ ጋር ሊለያዩ ከጫፍ መድረሳቸው ይፋ ሆኗል ።
• ማርኮስ ሮሆ የሰባት ዓመት የ ኦልድ ትራፎርድ ቆይታውን በማገባደድ ወደ አርጀንቲና ቦካ ጁኒየርስ ሊያመራ መሆኑ ይፋ ሆኗል ።
• በ አርጀንቲና ቦካ የህክምና ማዕከል ሁለቱ ቡድኖች በመለያየቱ ላይ ከስምምነት ሲደርሱ እንደሚያደርግ ተገልጿል ።
• በዩናይትድ ቤት ቀሪ የስድስት ወራት ጊዜ የሚቀረው ሮሆ ወደ ቦካ ጁኒየርስ በቋሚነት እንደሚዘዋወር ሲጠበቅ ያቀረቡት የ ሶስት ዓመት ኮንትራት ተቀባይነት እንደሚያገኝ ይጠበቃል ።
• የተጫዋቹ ወኪል ክርስቲያን ቤሪት በነገው ዕለት ወደ አርጀንቲና በማቅናት ከ ሮሆ ጋር በመነጋገር ዝውውሩን እንደሚያጠናቅቁ ተገልጿል ።