ለመጠናቀቅ የቀረቡ የተጫዋቾች ዝውውር

• ሳውዝሀምፕተን እና በርንማውዝ የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊት የተጫዋች ልውውጥ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል ።
• ሳውዝሀምፕተን ጆሹዋ ኪንግን ወደ ክለቡ ለማምጣት እየሰሩ ሲገኝ በተቃራኒው ሼን ሎንግ ወደ በርንማውዝ ለማቅናት በንግግር ላይ ናቸው ።
• ራልፍ ሀሰን ሁትል ተጫዋቹን ጆሹዋ ኪንግ ማሳመናቸው ሲገለፅ ኤቨርተን እና ፉልሀም ሌሎች የተጫዋቹ ፈላጊዎች ነበሩ ።
• በርንማውዝ የኪንግ ውል በመጪው ክረምት መጠናቀቁን ተከትሎ በዚህ የዝውውር መስኮት ለመሸጥ መገደዳቸው ተነግሯል ።
• ኤቨርተን አጥቂያቸውን ሴንክ ቶሱንን ለ ቤሽኪታሽ መስጠታቸውን ተከትሎ ወደ ገበያው ቢወጡ የ #FinancialFairPlay እንቅፋት እንደሆነባቸው ተገልጿል ።
• ኤቨርተን ይህ ዝውውር እንዲሳካ የ 19 ዓመቱን አጥቂያቸው አንቶኒ ጎርደን በውሰት ወደ በርንማውዝ እንዲዘዋወር ማቀዳቸው ተነግሯል ።
• ሌላኛው የተጫዋቹ ፈላጊ የሆኑት ፉልሀሞች በሊጉ የሚገኙበት የደረጃ ሰንጠረዥ ጆሽዋ ኪንግን አለማስደሰቱ ይፋ ተደርጓል ።
• የሼን ሎንግ በሳውዝሀምፕተን የመጫወቻ ጊዜ አለማግኘት ወደ በርንማውዝ ለማቅነት ከፍተኛ ፍላጎትን ሲያሳድርበት ዝውውሩ የመጠናቀቁ እድል ሰፊ መሆኑ ተጠቁሟል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.