በሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ወሳኝ ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን

በሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በደቡብ ሱዳን ተረታ

👉በሙሉ ዘጠና ደቂቃው ሀለቱም ባገኟቸው የፍጹም ቅጣትምቶች አንድ ለአንድ በማጠናቀቃቸው ወደተጨማሪ 30 ደቂቃ ለምራት የተገደዱ ሲሆን በተጨማሪውም ሰአት ሁለቱም አንዳንድ ጎል በማከላቸውና ሁለት አቻ በመጠናቀቁ የአቻ ውጤቱን ተከትሎ በተሰጠ የመለያ ምት ደቡብ ሱዳን 4ለ2 በማሸነፍ የውድድሩ የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኗ ተረጋግጧል።

👉ኢትዮጵያ 2-2 ደቡብ ሱዳን
⚽️9′ ዮሴፍ ታረቀኝ         ⚽️ 18′ ጆሴፍ ጄል
⚽️107′ ዘላለም አባተ    ⚽️111′ አጉዊምቦኪ አቢሻይ

👉 ደቡብ ሱዳን ከዩጋንዳ ጋር የፍፃሜ ተፋላሚ የሆነ ሲሆን በተጨማሪ በግብፅ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የአፍሪካ ዋንጫም ተሳታፊ ይሆናል።

👉 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ3 የደረጃን ለማግኘት ከውድድሩ አዘጋጅ ሱዳን ጋር የሚገጥም ይሆናል።

👉ከ 20ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ አዘጋጇ ሀገር ግብፅ ፣ ሴኔጋል ፣ደቡብ ሱዳን፣ ቤኒን ፣ ሞዛምቢክ እና ዛምቢያ፣ቱኒዚያ ፣ ጋምቢያ ፣ ናይጄርያ አስቀድሞ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.