አምራቾችን እና ሸማቾችን በቀላሉ የሚያገናኝ ፕላትፎርም ይፋ ሆነ!
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ኢትዮ ቴሌኮም
የአምራች ኢንዱስትሪዎችን እርስ በእርስ የሚያስተሳስር “ኢ-ታምርት” የተሰኘ የB2B የኢ-ኮሜርስ ፕላትፎርም ስራ አስጀምረዋል።

ይህ ወደ ዲጂታል ግብይት የሚያሸጋግር “ኢ-ታምርት” የተሰኘ ዘመናዊ B2B የኢ-ኮሜርስ ፕላትፎርም በዛሬው ዕለት በሳይንስ ሙዚየም
በይፋ የተጀመረ ሲሆን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል በመርሃግብሩ ላይ ፕላትፎርሙ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ከግብዓት አቅርቦት ጋር በተያያዘ የሚገጥማቸውን ችግር በመቅረፍ፣ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ምርቶቻቸውን ለሀገር ውስጥና ለአፍሪካ ገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስቸላቸው ነው ብለዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አቶ መላኩ ከዚህ በተጨማሪ በዘመናዊ የግብይት ስርዓት ያልተደገፈ አምራች ኢንዱስትሪ ውጤታማ አይሆንም ስለዚህ ፕላትፎርሙ የማምረት አቅምን በማሳደግ፣ ፈጠራን በማበረታታት እና የሀገራችንን ዘላቂ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማረጋገጥ ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል በማለት ለተሰበሰቡት የግልና የመንግስት ድርጅት ታዳሚዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን አያይዘውም
ኢ-ታምርት ሀገራችን ከሸማችነት ወደ አምራችነት ለምታደርገው ሽግግር ቁልፍ ሚና ከመጫወት ባሻገር፤ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። በመከፈቻው ስነስርአት ላይ የፕላት ፎርሙን አጠቃቀም እና ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ በማለሙያዎች
ሰፋ ያለ ገለጻ እና ማብራሪያ ተሰጥቶታል ።

ይህ አውደ ርዕይ እና የምዝገባ መርሐ ግብር በሳይንስ ሙዚየም እስከ ኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቀጥል መሆኑም የተገለጸ ሲሆን የግልና የመንግስት ድርጅቶችም አወደ ርእዩን በመጎብኘት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል።
✍️ፈለቀ ደምሴ
