ከተራራ ላይ ሆኖ ጨዋታ ያስተላለፈው ታዳጊ!

ከደቡባዊ ፔሩ ክፍል የተገኘው ክሊቨር ሁማን ሳንቼዝ የተሰኘ ታዳጊ ከሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኗል።

ክሊቨር የእግር ኳስ ዘጋቢ የመሆን ህልም ያለው የ15 አመት ታዳጊ ሲሆን በደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውን የኮፓ ሊበርታዶሬስ ዋንጫ ጨዋታ ለማስተላለፍ 18 ሰአታት ተጉዞ ወደፔሩ ዋና ከተማ ሊማ ያቀናል፤ሆኖም ወደስታድየም እንዳይገባ ተከለከለ።

እርሱ ግን ከስታድየም መከልከሉ ጨዋታውን እንዳያስተላልፍ አላደረገውም፤ ይልቁንስ በአቅራቢያው በሚገኝ ተራራ ላይ ወጥቶ ጨዋታውን በሞባይል ስልኩ እየቀረፀ አስተላፏል። ይህን ቀጥታ ስርጭትም በርካቶች ተመልክተውት ጉዳዩ የብዙዎችን ቀልብ ገዛ። በሚዲያዎችም ላይ ስለእሱ ይፃፍ ጀመር።

ይህን የተመለከቱት የፔሩ ሊግ ሰዎችም አንድ የፔሩቪያን ሊግ ጨዋታን እንዲያስተላልፍ ጋብዘውታል።

Photo credit: Four-Three-Three

ታሪኩ በዚህ ብቻ አላበቃም በቀጣይ ሳምንት ሪያል ማድሪድ ከ ማንቺስተር ሲቲ ሚያደርገውን ጨዋታ እንዲከታተል ተጋብዟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.