ኢትዮ ቴሌኮም በካሜሩን ታሪካዊ ስምምነት አደርገ!

ኢትዮ ቴሌኮም ከካምቴል (CAMTEL) ጋር በካሜሩን የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ተፈራርማል። ይህ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የሚያስችል ታሪካዊ የማስተር ሰርቪስ የኮንትራት ስምምነት በዛሬው እለት በካሜሩን ያውንዴ ሀጉራዊ ስምምነት አድርጓል!

የካምቴል የስራ ሃላፊዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢትዮ ቴሌኮም በ”ዲጂታል ኢትዮጵያ” ግንባታ ውስጥ ያሳየውን የላቀ የቴክኖሎጂ አመራር ከተመለከቱ በኋላ፣ ተሞክሮውን ወደ ካሜሩን ለመውሰድ ከነበራቸው ፍላጎት የመነጨ ነው ተብሏል።

በዚህም መሰረት ሁለቱ ኦፕሬተሮች በካሜሩን የፋይናንስ ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ለማስፋፋት፣ ብሄራዊ ክላውድ በመገንባት የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ፣ የሞባይል ኔትወርክ ጥራትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የካምቴልን አሰራር በይበልጥ በማዘመን ደንበኛ ተኮር ባህል ለመገንባት በጋራ ይሰራሉ የተባለ ሲሆን በተጨማሪም ስምምነቱ፤ ለካሜሩን የዲጂታል ኢኮኖሚ ቁልፍ የሆኑ ተቋማትና ቢዝነሶች የሚያቀላጥፉ ዲጂታል መፍትሄዎችን፣ የተጨማሪ እሴት እና የኢንተርኮኔክት አገልግሎቶችን በጋራ ለመተግበር ያስችላል በማለት ኢትዮ ቴሌኮም በድረ ገጹ ዘግቧል ።

ፈለቀ ደምሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.