ቅዱስ ጊዮርጊስ አማኑኤል ገብረሚካኤልን አስፈረመ

 

በሀገራችን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የተነሳ ዘንድሮ መቐለ በፕሪምየር ሊጉ መሳተፍ አጠራጣሪ በመሆኑ ፌድሬሽኑ ለዘንድሮው ዓመት ብቻ በሦስቱ የትግራይ ክልል ክለቦች ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾች በሌላ ክለብ ገብተው መጫወት ይችላሉ ባለው መሰረት የመቐለ 70 እንደርታው አጥቂ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ፈረሰኞቹን ተቀላቅሏል፡፡

በዛሬው ዕለት ፊርማውን ካኖረ በኃላ የኮቪድ 19 ምርመራን ያደረገው ተጫዋቹ አራት ዓመታት ያሳለፈበት ክለብን ለቆ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ መጓዙ ተረጋግጧል፡፡
የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሶስቱ የትግራይ ክለቦች የማይወዳደሩ ከሆነ ተጨዋቾቹ ወደፈለጉበት ክለብ እንዲገቡ በመፍቀዱ በቀጣዮቹ ቀናት የተጨዋቾች የፊርማ ዜና በብዛት ይሰማል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.