ሃዲያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን 2ለ1 አሸነፈ
ሶስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው በአንደኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ የወንዶች ፕሪምየር ሊግ ሃዲያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን 2ለ1 አሸነፈ
ወላይታ ድቻ በመጀመሪያ የጨዋታ ክፍል ጊዜ በ3ኛው ደቂቃ ላይ ቸርነት ጉግሳ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ችሎ ነበር፡፡
60ኛው ደቂቃ ላይ ግን ከግራ መስመር እየተነሳ በግሉ ክፍተት ለመፍጠር ሲጥር የነበረው ዳዋ ሆቴሳ ላይ ጥፋት ተሰርቶ ዳዋ ራሱ በቀጥታ በመምታት ድንቅ የቅጣት ምት ጎል በማስቆጠር ሃዲያ ሆሳዕናን አቻ ማድረግ ችሏል።
በአቻነቷ ጎል የተነቃቁት ሃዲያ ሆሳዕናዎች በዱላ ሙላቱ የማሸነፊያውንና ሁለተኛዋን ግብ በ79ኛው ደቂቃ ላይ በማስቆጠሩ ሃዲያ ሆሳዕና በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ 3 ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡
niccaso 1aedd1d5d3 https://wakelet.com/wake/KLrQukBb7oJm5HLypdfri