ወላይታ ዲቻ መቻልን 1 ለ 0 አሸነፈ።
ወላይታ ዲቻ መቻልን አሸነፈ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 10:00 ሰዓት በተካሄደዉ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ መቻልን 1 ለ 0 አሸነፈ። የወላይታ ዲቻን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል ቃልኪዳን ዘላለም በ31ኛዉ ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
በቀጣዩ 7ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር መቻል ከድሬዳዋ ከተማ ሀሙስ ህዳር 1 ምሽት 1:00 ሰዓት ላይ የሚጫወት ሲሆን ወላይታ ዲቻ ከለገጣፎ ለገዳዲ እሁድ ህዳር 4 ምሽት 1:00 ሰዓት ላይ ጨዋታዉን ያደርጋል።