በቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላለመውረድ  የሚደረገው ፉክክር እንደቀጠለ ነው።

23ኛው ሳምንት ላይ የሚገኘው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በባህርዳር ስቴዲየም መካሄዱን እንደቀጠለ ነው።

በእለቱ የተካሄደው ሁለተኛ (የ7 ሰአቱ) ጨዋታ።

▪️ሰበታ ከተማ 2-1 ጅማ አባ ጅፋር
20’⚽️ዴሪክ ንስባምቢ  7’⚽️መሐመድኑር ናስር
58’⚽️ አብዱላዚዝ ቶፊቅ(ፍ/ምት)

▪️ሁለቱም ወራጅ ቀጠናው ውስጥ የሚገኙ ክለቦች እንደመሆናቸው መጠን ጨዋታውን ለማሸነፍ ጥሩ ፉክክር አድርገዋል።

▪️ሰበታ ከተማ ከኋላ በመነሳት ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ሙሉ 3 ነጥቡን የግላቸው ማድረግ ሲችሉ የውድድር ዘመኑ 3ኛ ድላቸውን አስመዝግበዋል።

▪️ ጅማ አባጅፋር በ18ኛው ሳምንት በፋሲል ከተማ ሽንፈትን ካስተናገደ በኋላ ኢትዮጵያ ቡናን ነጥብ አስጥሎ ባህርዳር ከተማ እና አርባምንጭ ከተማን አሸንፈው መነቃቃት ቢያሳዩም በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ በሚገኘው ሰበታ ከተማ ሽንፈትን አስተናግደዋል።

▪️ውጤቱን ተከትሎ ሰበታ ከተማ ነጥቡን 17 ሲያደርስ ጅማ አባ ጅፋር በበኩሉ በ19 ነጥብ ከሰበታ ከተማ 1 ደረጃ በመብለጥ 15ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።

▪️ከጨዋታው በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️የጅማ አባ ጅፋር ምክትል አሰልጣኝ የሱፍ አሊ 🗣 ያገኘናቸውን አጋጣሚ አልተጠቀምንም ፣ የቀጣይ ጨዋታዎች የተሻለ ለመንቀሳቀስ እንሞክራለን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️የሰበታ ከማው ብርሀኑ ደበሌ በበኩላቸው 🗣 ውጥረት የነበረው ጨዋታ ነበር ግን አሸንፈን መውጣት ችለናል።ድላችን የዘገየ ቢሆንም ለቀጣይ ለምናደርጋቸው ጨዋታዎች ስንቅ እንዲሁም መነሳሳትን የሚፈጥር ነው። ብለዋል

▪️በቀጣይ ማለትም በ24ኛው ሳምንት መርሀ-ግብር ጅማ አባ ጅፋር ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ሰበታ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ሚካኤል ደጀኔ

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.