በባህር ዳር ስታዲየም ተሸንፎ የማያውቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ግዜ ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደቡብ አፍሪካ አቻው 3-1 ተሸነፈ።

በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተሸንፎ የማያውቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ግዜ ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡

በጨዋታው መጀመሪያ ደቡብ አፍሪካዎች ጫና ፈጥረው በመጫወት በኢትዮጵያ የግብ ክልል በተደጋጋሚ መድረስ የቻሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋጮች ኳስን በመቆጣጠር ባፋናዎች የፈጠሩትን ጫና በማቀዝቀዝ ኳሱን ተቆጣጥረው መጫወት የቻሉ ሲሆን ከሽመለስ በቀለ የሚጣሉ ኳሶችን በመቀበል የማጥቃት እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን በመጀመሪያው ግማሽ 20 ደቂቃዎች በሱራፌል ዳኛቸው አማካኝነት ኢላማቸውን ያልጠበቁ ሁለት ሙከራዎች አድርገዋል በ27ኛው በደቡብ አፍሪካ የቀኝ ሳጥን መግቢያ አካባቢ ረመዳን የሱፍ ከሲድኒ ሞቢ ያስጣለውን ኳስ ሱራፌል ዳኛቸው አክርሮ መትቶ ግብ ጠባቂው ሮን ዌን ዊልያምስ መልሶበታል።

ደቡብ አፍሪካዎች 33ኛው ደቂቃ ላይ ታቢሾ ኩቱሜላ ከግራ ወደ መሀል በመግባት የመታው ኳስ ወደ ውጪ የወጣበት ሲሆን በ37ኛው ደቂቃ ላይ የሱራፌል ዳኛቸው ያሻገረውን ኳስ አቡበከር ናስር አንድ ተከላካይ በማለፍ ወደ ግብ የላከውን ግሩም ኳስ ዊሊያም አድኖበታል በ39 ደቂቃ አቡበከር ከረመዳን ናስር የደረሰውኝ ኳስ ሰንጥቆ በመግባት በዊሊያምስ አናት ላይ የላከው ኳስ የባፋናው ግብ ጠባቂ አምክኖታል በ 45ኛ ደቂቃ ላይ ከፍጹም ቅጣት ሣጥን ውጪ ለባፋናዎቹ የተሰጠውን ቅጣት ሚት ቲቦኖ ሞኮና በቀጥታ ወደ ግብ የመታውን ኳስ የዋሊያዎቹ በረኛ ፋሲል ኳሱን ከያዘው በኋላ በመልቀቁ ግብ የተቆጠረ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን ባገኙት ወርቃማ ድል 1-0 መምራት ችለዋል።

በሁለተኛው እንደተጀመረ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የተሸለ ፈጣን እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን በ55ኛው የሱራፌል ዳኛቸው ከርቀት ወደግብ የላከው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል በ67ኛው ደቂቃ ከፍጹም ቅጣት ክልል ውጪ ሱራፌል ዳኛቸው ላይ በተሰራ ጥፋት የተገኘውን ቅጣት ምት ጌታነህ ከበደ በግሩም ሁኔታ አክርሮ በመምታት ባፋናዎቹ መረብ ላይ በማሳረፍ ዋሊያዎቹ አንድ አቻ እንዲሆኑ እንዲነቃቁ አስችሎ ነበር፡፡

ከአምስት ደቂቃዎች በኋላ ደቡብ አፍሪካዎች በረጅሙ ወደ ፊት የላኩት የእጅ ውርወራ ኳስ በዋሊያዎቹ ተከላካዮች እና በበረኛው ትኩረት ማጣት ባፋናዎቹ በአምንበላቸው ሞቶቢ ምቫላ አማካይነት ወደ ሁለተኛ ግብነት አስቆጥረዋል።
ከዚህ ግብ መቆጠር በኋላ የዋሊያዎቹን ትኩረት ማጣት እና ያለመናበብ የተረዱት የደቡብ አፍረካ ተጫዋቾች በ79ኛው ደቂቃ ላይም በኤቪደንስ ማጎፓ ከቀኝ መስመር የተላከለትን ኳስ በግንባር ገጭቶ የግቡ አንግል መልሶበታል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ መስፍን ታፈሰ እና እቤል ያለውን ቀይረው ያስገቡ ቢሆንም ዋልያዎቹን ከሽንፈት መታደግ አልቻሉም ይልቁንም የዋሊያዎቹን የአማካይ ቦታ እና የኋላ መስመር መዳከም የተረዱት ባፋናዎቹ በመልሶ ማጥቃት ኤቪደንስ ማጎፓ በረጅሙ የተላከለትንን ኳስ ለቪክቶር ሌትሶዋሎ አቀብሎት በድጋሚ ኳሱን ተቀብሎ በግብ ጠባቂው በፋሲል አናት ላይ ግብ በማስቆጠር የደቡብ አፍሪካ ቡድን በባህርዳር ስቴዲየም ተሸንፎ የማያቀውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 3ለ1 በማሸነፍ ደቡብ አፍሪካ በአለም ዋንጫ ማጣሪያው ነጥባቸውን ወደ ሰባት በማሳደግ የቻሉ ሲሆን ምድቡን መምራት የቻሉ ሲሆን ኢትዮጵያ ለጊዜው በሦስት ነጥቦች ሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በዚሁ ምድብ በተደረገ ሌላ ጨዋታ ጋና ዚምባቡዌን በተመሳሳይ 3 ለ 1 በማሸነፏ ምድቡን በሁለተኛ ደረጃ ይዛ ስትቀጥል ዚምባቡዌ በአራተኛ ደረጃ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጣለች።

1 .ደቡብ አፍሪካ 👉 7

2. ጋና 👉 6

3.ኢትዮጵያ 👉 3

4.ዚምባብዌ 👉 1

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.