የአውሮፓ ሻምፒዎንስ ሊግ የክለቦች የዕጣ ድልድል

👉 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የእጣ ድልድል እንደገና ተካሂዶ በጥሎ ማለፉ ማ ከማ ከማ ጋር እንደሚገናኝ አሳውቋል።

👉 በዚህም መሠረት
▪️ፒ ኤስ ጂ ከ ሪያል ማድሪድ

▪️ኢኔተርሚላን ከ ሊቨርፑል

▪️ቪላሪያል ከ ጁቬንትስ

▪️አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

▪️ቼልሲ ከ ሊል

▪️ቤኔፊካ ከ አያክስ

▪️ስፓርቲንግ ሊዝበን ከ ማንቸስተር ሲቲ

▪️ሳልዝበርግ ከ ባየርሙኒክ

እንደገና እጣው እንዲወጣ የተደረገበት ምክንያት
▪️1ኛ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቪላሪያል በአንድ pot ውስጥ ነበሩ። ይህ ደግሞ መሆን አይችልም ምክንያቱም እነዚህ ቡድኖች በምድብ 6 ተደልድለው እርስበእርስ ስለተጋጠሙ ተመልሰው መገናኘት አይችሉም።
▪️2ኛ ሊቨርፑል እና አትሌቲኮ ማድሪድ አሁንም በአንድ pot ውስጥ ነበሩ ሚል ነገር ሲሆን በአንድ ምድብ ተደልድለው ስለነበር ይህም ስህተት ነው።

▪️3ኛው እና የመጨረሻው ማንቸስተር ዩናይትድ በአትሌቲኮ ማድሪድ ተንተርሶ የወጣው ድልድል ላይ ሳይከተት መቅረቱ ስህተት ነው ሚል ነው።

አዲስ ከወጣው ድልድል በፊት የወጣው የምድብ ድልድል ላይ
psg ከ ማንቸስተር ዩናይትድ
አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ባየርሙኒክ ተገናኝተው ነበር።

ሜሲ እና ሮናልዶን በዩናይትድ እና በ psg ማልያ ለመጀመሪያ ጊዜ የማየት እድል እናገኝ ነበር ግን አልሆነም።

▪️ማንቸስተር ዩናይትድ ለመጨረሻ ጊዜ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር የተገናኙት እኤአ በ1991 ህዳር ወር ላይ ሲሆን ማንቸስተር ዩናይትድ በስፔኑ ክለብ በሁለተኛ ዙር ከውድድሩ ተሰናብቶ ነበር። አሁን ግን ክርሰቲያኖ ሮናልዶ በማንቸስተር ዩናይትድ መገኘቱ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ላይ ታሪክ የማይረሳቸው ግቦች አስቆጥሯል። ለመጥቀስ ያክል በ2014 የፍፁም ቅጣት ምት ለሪያል ማድሪድ አስቆጥሮ ነበር በ2015 በሩብ ፍፃሜው አትሌቲኮ ማድሪድ 1-0 ሲያሸንፎ ኳሱን አመቻችቶ ማቀበሉ በ2016 የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ የመጨረሻ የፍፁም ቅጣት ምቱን ማስቆጠሩ በ2017 በግማሽ ፍፃሜው 3ጎሎችን አትሌቲኮ ማድሪድ መረብ ላይ ማሳረፉ እንዲሁም በ2019 ለጁቬንትስ እየተጫወተ አትሌቲኮ ማድሪድን 3ግቦችን በማስቆጠር ከሩብ ፍፃሜው እንዲሰናበቱ ማድረጉ ይታወሳል። ስለዚህ ማንቸስተር ዩናይትድ አሁንም በሮናልዶ ታግዞ ሩብ ፍፃሜውን ይቀላቀል ይሆን ሚለው ተጠባቂ ነው።

▪️ኢንተርሚላን ከሊቨርፑል ጋር 4 ጊዜ በአውሮፓ ጨዋታዎች የተገናኙ ሲሆን ናራዙሪዎቹ 1 ጊዜ ብቻ ነው ማሸነፍ የቻሉት 3 ጊዜ ደግሞ ቀያዮቹ አሸንፈዋል። የሁለቱም ቡድኖች አሁን ያሉበት አቋም ጥሩ መሆን ይህን ጨዋታ ተጠባቂ ያደርገዋል።

▪️ፓሪስ ሴንት ጄርሜ ከሪያል ማድሪግ ጋር የተደለደለ ሲህን ሲገናኙም ለ4ኛ ጊዜ ነው። በ1992/93 እና በተከታዩ አመት በ1993/94 ፓሪሶች ነጫጮቹ ሎስብላንኮዎቹን ሪያል ማድሪድን ከውድድሩ ውጪ ሲያደርጓቸው በ2017/18 ሪያል ማድሪዶች የፈረንሳዩን ሀያል ክለብ ፓሪስ ሴንጅ ጄርሜን ከውድድሩ ማሰናበታቸው ይታወሳል። ሜሲ እና ሰርጂዮ ራሞስ አንድላይ በመሆን ሪያል ማድሪድን ሚፋለሙበት መድረክ ይሆናል። ሊዮኔል ሜሲ ከሪያል ማድሪግ ጋር ሲገናኝ ጥሩ ታሪክ አለው በእግርኳስ ዘመኑ ሪያል ማድሪድን 45 ጊዜ የገጠመ ሲሆን 26 ጊዜ ጎል ሲያስቆጥር _4 ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።ሰርጂዮ ራሞስም ያለኝን አቅም ሁሉ አሟጥጬ ለፒ.ኤስ.ጂ ማበረክትበት ጨዋታ ነው ይህናል ሚል አስተያየት ሰጥቷል።ኪሊያን ምባፔም ስሙ በተለይ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ሪያል ማድሪድ ያቀናል ሚሉ ዘገባዎች በተደጋጋሚ ይወጡ ነበር። ልጁ አሁንም ኮንትራቱን አላደሰም ለማደስም ዝግጁነትእና ፍላጎት አይታይበትም ግን ፓሪስ ሴንት ጄርሜን ማልያ በመልበስ ልቡ የሸፈተበት ክለብን በተቃራኒ የሚገጥም ይሆናል።

የዩሮፓ ሊግ ዕጣ ድልድልም ይፋ ሆኗል።
▪️ሲቭያ ከ ዳይናሞ ዛግሬቭ
▪️አታላንታ ከ ኦሎምፒያኮስ
▪️ሌፕዚግ ከ ሪያል ሶሲዳድ
▪️ባርሴሎና ከ ናፖሊ
▪️ዜኒት ከ ሪያል ቤቲስ
▪️ዶርትሙንድ ከ ሬንጀርስ
▪️ሼሪፍ ከ ብራጋ
▪️እንዲሁም ፖርቶ ከ ላዚዮ ተደልድለዋል።

ሚካኤል_ደጀኔ

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.