የዝውውር ዜናዎች :-ኩን አግዌሮ ፣ ሀላንድ ፣ ሄክተር ቤለሪን ………

ባርሴሎና ፣ ፒኤስጂ ፣ ጁቬንቱስ እና ኢንተር ሚላን የሰርጂኦ ኩን አግዌሮ ፈላጊዎች ናቸው
ዘ ሚረር እንዳለው ከሆነ አርጀንቲናዊው ኮከብ በክለቦቹ ይፈለጋል። ተወካዮቻቸውም ፈላጎታቸውን አንስተው መገዛት እንደሚችል ጥቄዎችን እየተየቁ ነው። ተጫዋቹም የኮንትራቱ የመጨረሻ ጊዜያት ላይ ይገኛል በኢትሀድም ኮንትራት አልቀረበለትም።

ባዲያሺሌ ማንችስተር ዩናይትዶች አናግረውኝ ነበር አለ
የሞናኮው የመሀል ተከላካይ ቤኖይት ባዲያሺሌ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከማንችስተር የዝውውር ጥያቄ ቀርቦለት እንደነበር ገልጿአል በ2019/20 ባሳየው ድንቅ ብቃት ምክንያት በብዙ ክለቦች አይን ውስጥ የገባው ተጫዋቹ 19 አመቱ ሲሆን ሞናኮን በእጅጉ እያገለገለ ይገኛል።

ቼልሲ ሀላንድ ላይ አተኩሯል
ቱቶ መርካቶ በዌብሳይቱ ላይ እንዳሰፈረው ከሆነ ሃላንድ የቼልሲ ዋነኛ አላማ እንደሆነ ገልጿል ሮማን አብረሀምኦቪች ተጫዋቹን ባጣም እንደሚፈልጉት እና እንደሚያደንቁትም ገልጾአል።

ማት ዶርቲ ሊሸጥ ይችላል
ኢ.ኤስ.ፒ.ኤን እንዳለው የተጨዋቹ የቶተንሀም ቆይታ በ1 አመት ሊገታ ይችላል ብሎአል ቀኝ ተመላላሹ በ2020 ነበር ጆዜን የተቀላቀለው።

ሄክቶር ቤለሪን ወደ ፒ.ኤስ.ጂ ለመሄድ አኮብኩቧል
ባለፈው ዝውውር ፒኤስጂ ተጫዋቹን ማናገሩ ለተጫዋቹ ፍላጎት መጨመር ምክንያት ሆኖአል ይላል ሲ.ቢ.ኤስ ስፖርት። በ2020 ሊወስዱት ሞክረው በሚካኤል አርቴታ ሀይል ነው የቀረው ሚለው ሲ.ቢ.ኤስ ባርሴሎና እና ሌሎች የጣሊያን ክለቦች ፈላጊዎቹም ናቸው ከ6 ወር በፊትም 28.8 ዩሮ ለአርሰናል ቀርቦለት ነበር፡፡

አርሰናል ለሄክተር ቤለሪን ተተኪ አዘጋጅቷል ተባለ
ፉትቦል ዶት ለንደን እንዳለው ተጫዋጩ ክለቡን ሚለቅ ከሆነ በቦታው የኖርዊቹን ማክስ አሮንን ወይም የብራይተኑን ታሪቅ ላምፕቲ ሊተኩ ያስባሉ።

ቶኒ ክሮስ አላባ ለማድሪድ ሚመጥን ኮከብ ነው ሚል አስተያት ሰጠ
ከባየርን ሙኒክ ሚለቅ ከሆነ አላባ ለማድሪድ ድንቅ ብቃቱን ያሳያል ያለው ቶኒ የአላባን የባለፈው ሳምንት አስተያት ተከትሎ ነው አላባም ከባየርን ሙኒክ ጋር እንደማይቆይ አሳውቋል መሄጀውን ግን ይፋ አላወጣም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.