ድሬደዋ ከተማ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ተቀዳጀ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን በዛሬው ዕለት 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ለድሬዳዋ ከተማ አስቻለው ግርማ 41′ እና ጁኒያስ ናንጃቤ 84′  ጎል በማስቆጠር ድሬደዋ ከተማብ በቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪሜርሊግ የመጀመሪያ ድሉን መቀዳጀት ሲችል ጅማ አባ ጅፋር ደግሞ ለሶስተኛ ጊዜ ሽንፈትን አስተናግዷል።
ድሬደዋ ከተማ ሁለት ጊዜ ሲሸነፍ አንድ ጊዜ አቻ ወቷል፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በማሸነፍ ባጠቃላይ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በአራት ነጥብ እና በአንድ የጎል እዳ በስምንተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ጅማ አባ ጅፋር ደግሞ በሶስት ጨዋታዎች ተሸንፎ በአንድ ጨዋታ አቻ ወቷል። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥም በአንድ ነጥብ እና በስምንት የጎል እዳ በ12ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.