ሀዲያ ሆሳዕና ሲዳማ ቡናን 3ለ1 አሸነፈ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ሦስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ሲዳማ ቡናን 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ለሀዲያ ሆሳዕና አይሳክ አሴንዴ በ14ኛው፣ ሳለፉ ፎፎና በ48ኛው እና 56ኛው ደቂቃ ላይ ጎል ሲያስቆጥሩ ለሲዳማ ቡና የማስተዛዘኛዋን ጎል ጊት ጋትኮች አስቆጥሯል።

የሶስተኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ መጠናቀቅ ተከትሎ ሃድያ ሆሳዕና በዘጠኛ ነጥብ እና በአራት የጎል ልዩነት በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዝ በአንደኝነት መቀጥ ችሏል። ሊጉን ሲመራ የነበረው ኢትዮጲያ በሰባት ነጥብ እና በአራት የጎል ልዩነት በደረጃ ሰንጠረዙ በሁለተኛ ደረጃነት ሲቀመጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በስድት ነጥብ እና በአራት የጎል ልዩነት በሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

የሊጉ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የፊታችን ሰኞ የሚቀጥል ሲሆን፣ ሰበታ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ይጫወታሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.