ወልቂጤ ከተማ ባህርዳር ከተማን 1ለ0 አሸንፏል
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወልቂጤ ከተማ ባህርዳር ከተማን 1ለ0 አሸንፏል።
ለወልቂጤ ከተማ ቶማስ ስምረቱ በመጀመሪያው መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በ31ኛው ደቂቃ የመጀመሪያዋንና ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።
ወልቂጤ ከተማ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን ባስመዘገበበት አራተኛ ሳምንት የቤት ኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ ሶስት ነጥቦችን ያገኘ ሲሆን በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥም በስምንት ነጥብ እና በሁለት የጎል ልዩነት በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ባህርዳር ከተማ ደግሞ በስድስት ነጥብ በሁለት የጎል ልዩነት ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።