በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር ያለምንም ግብ 0ለ0 ተለያዩ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር ያለምንም ግብ 0ለ0 ተለያዩ።
ሲዳማ ቡና በተከታታይ ሳምንታት ነጥብ እየጣለ የመጣ ሲሆን በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥም ከታች አንድ ደረጃ ከፍ በማለት በአንድ ነጥብ እና በአራት የጎል እዳ በ12ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። አዳማ ከተማ በአንፃሩ ደግሞ በአራት ነጥብ እና በአንድ የጎል እዳ በደረጃ በዘጠንኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።