ገንዘቤ ዲባባ በስፔን ባርሴሎና ሪከርድ ልትሰብር እንደምትችል ቅድሚያ ግምት አግኝታለች

ገንዘቤ ዲባባ ሪከርድ ለመስበር  በባርስሎና ላይ ትሮጣለች!

ኢትዮጵያዊቷ ገንዘቤ ዲባባ በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው ዓመታዊ የኩርሳ ዴልስ ናሶስ የ5 ኪ.ሜትር ውድድር ታናሽ እህቷን አና ዲባባ በአሯሯጭነት አስከትላ ሪከርድ ለመስበር ትሮጣለች።

ገንዘቤ ከአራት ሳምንት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የቫሌንሲያ የግማሽ ማራቶን ውድድር በ1 :05 :16 አዲስ ሪከርድ መስበሯ ይታወሳል።

የ5 ኪሎ ሜትሩ ርቀት በትውልድ ኢትዮጵያዊት በዜግነት ሆላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን (14:44) የተያዘ ሲሆን ገንዘቤ የ 5 ኪ.ሜ የነገውን ውድድር አዲስ ሪከርድ ታስመዘግባለች በሚል ከበርካቶች የቅድሚያ ግምት ተሰጥቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.