ሊዮኔል ሜሲ ለአንድ ክለብ ከፍተኛ ጎል የማስቆጠር ክብረወሰንን አሻሻለ

ሊዮኔል ሜሲ ለባርሴሎና 644ኛ ጎሉን በማስቆጠር ለአንድ ክለብ ከፍተኛ ጎል በማስቆጠር በፔሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሻለ።

አርጄንቲናዊው አጥቂ ትናንት ምሽት ሪያል ቫያዶሊድ ከባርሴሎና ባደረጉት የስፔን ላሊጋ የባርሴሎናን ሶስተኛ ግብ በ65ኛው ደቂቃ ላይ በማስቆጠር የፔሌን ክብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል። ሜሲ የከፍተኛውን ግብ ክብረ ወሰን በእጁ ለማስገባት የቻለው ቡድኑ ባርሴሎና ከሪያል ቫላዶሊድ ጋር በነበረው ግጥሚያ ላይ ከመረብ ያገናኘው ጎል ነው።

በዚህም ሜሲ ለአንድ ክለብ ብዙ ጎሎች በማስቆጠር የብራዚላዊውን እግር ኳሰኛ ፔሌ ክብረ ወሰን ሰብሯል። የ33 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ባርሴሎና ሪያል ቫላዶሊድን ባሸነፈበት ጨዋታ ከክለብ አጋሩ ፔድሪ የተቀበላትን የቅንጦት ኳስ ወደ ጎል ቀይሮ ነው ክብረ ወሰኑን የጨበጠው።

ብራዚላዊው የእግር ኳስ ጥበበኛ ፔሌ ለሳንቶስ ክለብ ከ1956 እስከ 1974 ተጫውቷል። ለ19 የውድድር ዘመኖች ለአገሩ ክለብ የተጫወተው ፔሌ 643 ጎሎች ከመረብ ማገናኘት ችሏል።

ብራዚላዊው ኮኮብ ፔሌ ከፈረንጆቹ 1956 እስከ 1974 ድረስ ከሃገሩ ክለብ ሳንቶስ ጋር በነበረው ቆይታ 643 ግቦችን አስቆጥሮ ነበር።

ሊዮኔል ሜሲ ለባርሴሎና የመጀመሪያውን ግብ በፈረንጆቹ 2005 ያስቆጠረ ሲሆን ከክለቡ ጋር 10 የስፔን ላሊጋ እና አራት የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል።

 አጥቂው በአሁኑ ወቅት ከክለቡ ጋር ያለው ውል እየተገባደደ ነው። በሚቀጥለው ጥር ከሚፈልጉት ክለቦች ጋር መደራደር ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.