ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃዋሳ ከተማን አሸነፈ

በሶስተኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየርሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃዋሳ ከተማን 4-1 አሸንፏል።

የፈረሰኞቹ የበላይነት በታየበት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ በሁለቱም ተጋጣሚዎች መካከል ቀዝቀዝ ያለ አጨዋወት ቢታይም ፈረሰኞቹ ሶስት ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል።

⚽️33′ ሮቢን ንጋላንዴ

⚽️39′ ጌታነህ ከበደ (ፍ)

⚽️43′ ጌታነህ ከበደ

⚽️ 80′ ብሩክ በየነ (ፍ) ባስቆጠሯቸው ጎሎች ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲያሽንፍ ያድረጉ ሲሆን ⚽️55′  የቅዱስ ጊዮርጊሱ ዳዊት ታደሰ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ጎል ሃዋሳ ከተማዎች በዜሮ ከመሸነፍ ድነዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃዋሳ ከተማን ማሸነፉ ተከትሎ የፕሪምየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ በስድስት ነጥብ እና በአራት የጎል ልዩነት እየመራ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.