ኢቶጲያ ቡና ድሬደዋ ከተማን አሸንፎ የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት ችሏል
በሶስተኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ በመጀመሪያ ቀን ሁለተኛ ጨዋታ ኢትዮጲያ ቡና እና በድሬደዋ ከተማ መካከል የተካሄደ ሲሆን በኢትዮጲያ ቡና 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ኢትዮጲያ ቡና የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታውን ካሸነፈ በኋላ በድጋሜ የደረጃ ሰንጠረዙን በሰባት ነጥብ እና በሶስት የጎል ልዩነት ሲመራ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በስድስት ነጥን እና በበአራት የጎል ልዩነት በሁለተኝነት ይከተላል።
አምስት ጎሎችን ያስተናገደው የኢትዮጲያ ቡና እና የድሬደዋ ከተማ ጨዋታ
⚽️9′ ሀብታሙ ታደሰ
⚽️55′ አማኑኤል ዮሐንስ
⚽️84′ ሀብታሙ ታደሰ ለኢትዮጲያ ቡና ጎል ሲያስቆጥሩ፤ ⚽️26′ ኬሙይኔ፣ ⚽️88′ ዘነበ ከበደ (ፍ) ደግሞ ለድሬደዋ ከተማ ጎል አስቆጥረዋል