ከዝውውሮቹ በስተጀርባ ያሉ መረጃዎች
• ሊቨርፑል ቤን ዴቪስን በ 1.6 ሚልዮን ፓውንድ ዋጋ ከ ፕሪስተን ሲያስፈርሙ የመርሲሳይዱ ክለብ በተቃራኒው ሴፕ ቫን ደን በርግን በውሰት ለፕሪሰተን ሰጥተዋል ።
• ቤን ዴቪስ በአመቱ መጨረሻ ከ ኮንትራት ነፃ መሆኑን ተከትሎ የስኮትላንዱን ሴልቲክ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሶ ነበር ።
• ቤን ዴቪስ ለ ፕሪስተን 135 ጨዋታዎችን ከ 2017/18 የውድድር ዓመት አንስቶ በቋሚነት ማድረግ ችሏል ።
• ሜትላንድ ኒልስ በ ሳውዝሀምፕተን እና ሌስተር ሲቲ በጥብቅ ቢፈለግም ክለቡ አርሴናል ተቀናቃኝ ክለቦችን ለማጠናከር ባለመፈለግ ወደ ዌስት ብሮም እንዲያቀና አድርገውታል ።
• አርሴናል ኒልስ ወደ ሳውዝሀምፕተን እንዲያቀና ቢፈልጉም ክለቡ በአመቱ መጨረሻ ተጫዋቹን ለመግዛት መፈለጋቸው ዝውውሩ እንዳይሳካ አድርጎታል ።
• የማርቲን ኦዴጋርድ መምጣት ቦታውን እንደሚያሳጣው የታመነው ጆ ዊሎክ ወደ ኒውካስትል ሊያመራ አስችሎታል ።
• ዊሎክ በአርሴናል ቤት የሊጉን የመጀመሪያ ጨዋታ ማድረግ የቻለው ከ አዲሱ ክለቡ ኒውካስትል ጋር ነበር ።
• ታኩሚ ሚናሚኖ ወደ ሳውዝሀምፕተን በውሰት ሲያቀና የተጫዋቹን ደሞዝ ጨምሮ የውሰት ክፍያ ሳውዝሀምፕተን እንደሚሸፍኑ ተገልጿል ።
• ሚናሚኖ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ለ ሊቨርፑል ስምንት ጨዋታዎችን ብቻ ማካሄድ ችሏል ።
• ሳውዝሀምፕተን የውሰት ውሉ ሲጠናቀቅ ተጫዋቹን የግላቸው ማድረግ ቢያልሙም በ ክሎፕ ተቀባይነትን አላገኘም።