ሊቨርፑል ተጨማሪ ተከላካይ አስፈርሟል

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የሻልኩን የመሐል ተከላካይ ኦዛን ካባክን ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል ።
• የመሀል ተከላካዩ ሊቨርፑልን እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ በውሰት ሊቀላቀል ችሏል ።
• ሊቨርፑል ለውሰት ዝውውሩ ክፍያ አንድ ሚልዮን ፓውንድ የሚከፍሉ ሲሆን በተጨማሪ በጉርሻ መልክ 500,000 ፓውንድ ለተጫዋቹ ይከፍላሉ ።
• ሊቨርፑል በ ኮንትራቱ መጨረሻ ኦዛን ካባክን በ 18 ሚልዮን ፓውንድ የግላቸው ማድረግ ይችላሉ ።
• በተከላካይ ቀውስ ውስጥ የሚገኙት ሊቨርፑሎች ትልቅ ዕረፍት ሲሆን በተለይም በ ሻልክ ቤት ያሰለጠኑት ዴቪድ ዋግነር ለ ክሎፕ ተጫዋቹን እንዲያስፈርሙት ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸው ተገልጿል ።
• ቱርካዊው ካባክ በ ሻልክ በሊጉ ከ 4,000 ደቂቃዎች በላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.