” ሜሲ በ ባርሳ ይቆያል የሚል ሙሉ እምነት የለኝም ” አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማን

ሰፋ ያለ ቆይታን ከ ጋዜጠኞች ጋር ማድረግ የቻሉት የ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማን የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተዋል ።
ከ እነዚህም መካከል :-
• ሊዮኔል ሜሲ 8 ለ 2 በተሸነፈው የቡድን ስብስብ ውስጥ ለመቀጠል ደስተኛ አልነበረም ፣ ክለቡን መልቀቅ ይፈልግ ነበር ።
• ነገሮችን እንድፈታ ብጠየቅም ችግሩ በክለቡ እና በተጫዋቹ መካከል ያለ መሆኑን በመናገር እራሴን አግልዬ ነበር ።
• ክለቡ ምንም አይነት ዝውውሮችን በሜሲ ዙርያ እንደማይቀበል እና በክለቡ መቆየት እንዳለበት የደመደመ ሲሆን ለሜሲ ከባድ ጊዜ ነበር ።
• የውድድር ዓመቱን ከመጀመራችን አስቀድሞ ሜሲን በመኖሪያ ቤቱ በመገኘት አውርቼው ነበር ።
• እቅዶቼን ለሜሲ ስነግረው ደስተኛ እና ተነሳሽነት ላይበት ችያለው ።
• በክለቡ ይቀጥላል የሚል ሙሉ እምነት የለኝም ይቆያል ብዬ ግን ተስፋ አደርጋለው ።
• የክለቡን የወደፊት ቀጣይ እጣ ፋንታ የሚያስቀጥል ፕሬዝዳንት ያስፈልገናል ።
• የዘንድሮው የውድድር ዓመት የሽግግር ጊዜ እንደመሆኑ ዋንጫ ማንሳት አይጠበቅብኝም ፣ ክለቡን ይህን ዋንጫ ማሳካት አለብክ ያለኝ አንዳችም ነገር የለም ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.