ወልቂጤ ከተማ ወላይታ ዲቻን 2ለ1 አሸነፈ

በተከታታይ ለሁለት ሳምንት በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ድል ያልቀናው ወልቂጤ ከተማ  ሦስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር  ወላይታ ዲቻን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፎ የመጀመሪያ ድሉን ተቀዳጅቷል።
ለወልቂጤ ከተማ ያሬድ ታደሰ ሁለቱን ጎሎች በ37ኛው እና በ65ኛው ደቂቃ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን  እንድሪስ ሰዒድ ደግሞ ለወላይታ ዲቻ ብቸኛዋን ጎል በ74ኛው ደቂቃ በማስቆጠሩ ጨዋታው 2ለ1 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ወልቂጤ ከተማዎች አምስት ነጥቦችን በመያዝ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወላይታ ዲቻ ደግሞ ሶስት ነጥብ በማግኘት ዘጠንኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.