ፋሲል ከነማ ጅማ አባጅፋርን 4ለ1 አሸነፈ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ሦስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ጅማ አባጅፋርን 4ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለፋሲል ከነማ በ38′ አምሳሉ ጥላሁን፣  በ41′ ሙጂብ ቃሲም ቃሲም በመጀመሪያው አጋማሽ ግብ ማስቆጠር ችለዋል።

በሁለተኛው መደበኛ የጫወታ ክፈለ ጊዜ ሳሙኤል ዮሐንስ ለፋሲል ከነማ በ76′ 3ኛዋን ግብ ከመረብ ሲያሳርፍ ሽመክት ጉግሳ በ86ኛው ደቂቃ 4ኛውን ግብ አክሏል።
ጅማ አባጅፋር ብቸኟዋን ግብ በብዙዓየሁ እንደሻው በ72ኛው አስቆጥሯል።

የጅማ አባ ጅፋር እና የፋሲል ከነማ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ በፕሪሜርሊጉ ውስጥ ያላቸውን ደረጃ መቀየር ችለዋል በዚህም ፋሲል ከነማ በስድስት ነጥብ እና በሁለት የጎል ልዩነት በሶስተኛ ደረጃ ሲቀመጥ ጅማ አባ ጅፋር ደግሞ በአንድ ነጥብ እና በስድስት የጎል እዳ በአስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.