የሊግ ኩባንያው የልዑካን ቡድን ወደ ጅማ ከተማ ሊያቀና ነው

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አወዳዳሪ አካል የሆነው ሊግ ኩባንያው የልዑካን ቡድን ወደ ጅማ ከተማ ሊልክ እንደሆነ ተሰምቷል።

የ2013 የውድደር ዘመን በቤትኪንግ ስፖንሰር አድራጊነት የቀጥታ የቴሌቭዥን ሽፋን አግኝቶ መካሄድ ከጀመረ ሁለት ሳምንታትን አስቆጥሯል። በአምስት በተመረጡ ከተሞች የሚካሄደው የዘንድሮው ውድድር የመጀመርያዎቹን ስድስት ሳምንት ጨዋታዎች እንድታስተናግድ የተመረጠችው አዲስ አበባ እስካሁን ጨዋታዎቹን በመልካም ሁኔታ እያስተናገደች ትገኛለች። በቀጣይነት ከሰባተኛ እስከ አስራ አንደኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎችን ለማካሄድ የተመረጠችው ደግሞ ጅማ ከተማ መሆኗ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ የሊግ ካምፓኒው የጅማ ከተማ የሆቴል፣ የውድድር እና ልምምድ ሜዳዎች እና አጠቃላይ ቅድመ ዝግጅቱን አስመልክቶ ግምገማዎችን ለማድረግ የልዑክ ቡድኑ በቅርቡ ወደ ሥፍራው ያቀናል። ከጉብኝቱ በኋላ የልዑክ ቡድኑ ምን ዓይነት ምላሽ ይዞ ይመጣል የሚለው በቀጣይ የሚጠበቅ ዐበይት ጉዳይ ይሆናል ሲል ሶከር ኢትዮጲያ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.