ሊንጋርድ ዳግም ወደ ለንደን ሊመለስ ነው
ኢንግሊዛዊው ጄሴ ሊንጋርድ ዳግም ዌስትሀም ለማቅናት ተቃርቧል ።
ሊንጋርድ ከዚህ ቀደም በውሰት ዌስትሀምን ተቀላቅሎ ድንቅ ብቃቱን አሳይቶ እንደነበረ ይታወሳል ።
የጣሊያኑ ክለብ ኤሲ ሚላን ሌላኛው የጄሴ ሊንጋርድ ፈላጊ ቢሆንም ዌስትሃሞች ግን 29 አመቱን ኢንግሊዛዊ ለማስፈረም ንግግር ጀምረዋል ።
በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት የቋሚነት እድሉ የተነፈገው ሊንጋርድ ከማን ዩናይትድ ጋር 1 የዩሮፖ ሊግ ፣ 1 የኤፍ ኤ ካፕ ፣ 1 የሊግ ካፕ እና 1 የኢንግሊዝ ኮምኒቲ ሽልድ ዋንጫ ማሳካት ችሏል ።