የ18ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ
ትናንት በተደረገ 18ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌትሪክ ከ ድሬደዋ ከተማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል ።
8 ሰዓት ሲል የተጀመረው የአርባ ምንጭ ከተማ እና አቃቂ ቃሊቲ ጨዋታ በአርባ ምንጭ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል ።
በጨዋታው በድንቅነሽ በቀለ ሁለት ግቦች እና ወርቅነሽ ሜልሜላ ግብ ታግዘው አርባ ምንጭ ከተማዎች 3 ለ 0 በሆነው ውጤት አሸንፈዋል ።
ሌላኛው ከባድ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ የተጠበቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የመከላከያ ጨዋታ በልማደኛዋ ሎዛ አበራ ግብ ኢትዮጵያ ንግድ ማሸነፍ ችሏል ።
በደረጃ ሰንጠረዡም አትዮጵያ ንግድ ባንክ በ48 ነጥብ ሲመራ በሁለተኝነት ደግሞ ሀዋሳ ከተማ በ38 ነጥብ በመያዝ ይከተላል ። ኢትዩ ኤሌትሪክ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው በ37 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዟል ።
በውድድሩ 29 ግብ በማስቆጠር ሎዛ አበራ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆናለች ። ሴናፍ ዋቁማ ከመከላከያ በ14 ግብ ትከተላለች ።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዓርብ ሀምሌ አንድ ሲቀጥል
3:00 ድሬደዋ ከተማ ከ ባህር ዳር ከተማ
8:00 አቃቂ ቃሊቲ ከ ኢትዮ ኤሌትሪክ
10:00 መከላከያ ከ አርባምንጭ ከተማ
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋሉ ።