ኢትዮጵያዊያን የደመቁበት የደሊሂ ግማሽ ማራቶን ውድድር
በደሊሂ ግማሽ ማራቶን (ህንድ) ኢትዮጵያዊው አምደወርቅ ዋለልኝ 58:53 በመግባት የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል አሸንፏል።
አምደወርቅ ዋለልኝን በመከተል አንዱ አምላክ በልሁ 2ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ጠንካራው አትሌት ሙክታር ኢድሪስ 4ኛ ሆኖ አጠናቋል ።
የህንድ ደሊሂ ግማሽ ማራቶን በሴቶችም ሲደረግ የቦታውን ሰአት በማሻሻል ኢትዮጵያዊቷ ያለምዘርፍ የኃለው አሸንፋለች ።
ያለምዘርፍ የኃለው 64:46 በመግባት የቦታውን ሪከርድ መስበር ችላለች ።
በውድድሩም ኢትዮጵያኖቹ አባበል የሻነው 3ኛ እና ፀሀይ ገመቹ 5ኛ በመሆን ጨርሰዋል ።