ድሬዳዋ ከተማ ወላይታ ዲቻን 2ለ1 አሸነፈ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ወላይታ ዲቻን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ለድሬዳዋ ከተማ አስቻለው ግርማ በ13ኛው ደቂቃ እና ሙህዲን ሙሳ በ36ኛው ደቂቃ ጎል አስቆጥረዋል። ለወላይታ ዲቻ ብቸኛዋን ግብ ፀጋዬ ብርሀኑ በ34ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ ረፋድ ላይ ወላይታ ድቻን በማሸነፍ የውድድር ዘመኑን ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ድሬደዋ ከተማ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በአራት ነጥብ እና በአንድ የጎል እዳ በስምንተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወላይታ ዲቻ ደግሞ በሶስት ነጥብ እና በአንድ የጎል እዳ በ11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የሊጉ አምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ከሰዓት ሲቀጥል 9 ሰዓት ላይ ባህርዳር ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር እንደሚጫወቱ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።
