በሀዋሳ እየተካሄደ ባለው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የውድድሩ ሪከርድ የተሻሻለበት ውጤት ተመዘገበ።
👉 3ኛው ቀኑን በያዘው 51ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው ውሎ በርካታ ውድድሮችን አካሂዷል።
👉በሴቶች ዘርፍ በተካሄደ የምርኩዝ ዝላይ የፍፃሜ ውድድር።
▪️ሲፈን ሰለሞን ከ ጥሩነሽ ዲባባ 2.10 ከፍታ በመዝለል 1ኛ ስትሆን
▪️ሜቲ ቤኩማ ከ ጥሩነሽ ዲባባ 2.00 ከፍታ በመዝለል ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
👉በወንዶች በተካሄደ የዲስከስ ውርወራ ፍፃሜ ውድድር።
▪️ ማሙሽ ታየ ከ ሲዳማ ቡና 45.09 ርቀት በመወርወር የውድድሩን ሪከርድ በማሻሻል ጭምር በአንደኝነት ሲያጠናቅ
▪️ገበየሁ በ/ኢየሱስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 43.77 ሜትር በመወርወር 2ኛ እንዲሁም
▪️ ኢብሳ ገመቹ ከ አዳማ ከተማ 42.85 ሜትር በመወርወር 3ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።
👉 በሴቶች የርዝመት ዝላይ ውድድር
ኪሩ ኢማን ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 5.75 ርቀት በመዝለል አንደኛ
▪️ማሬዋፒዶ ከመከላከያ 5.68 ርቀት 2ኛ እንዲሁም
▪️አርያት ዴቪድ ከ ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ 5.68 ርቀት በመዝለል 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

👉 በወንዶች በተካሄደ የ110 ሜትር መሰናክል ውድድር
▪️ማረሰ ተስፋዬ ከ ኢትዮጵያ ንግድባንክ 14.06 በመግባት ቀዳሚ
▪️ኬሪዮን ሞርቴ ከ ኦሮሚያ ክልል 14.43 ሁለተኛ እንዲሁም
▪️ሮድቾል ከ ጥሩነሽዲባባ ማሰልጠኛ 14.76 ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
👉በሴቶች 100 ሜትር መሰናክል ውድድር
▪️ሂርጰ ድርባ ከኦሮሚያ ክልል 14.08 በመግባት ቀዳሚ
▪️አለሚቱ አሰፋ ከኦሮሚያ ክልል 14.17 በመግባት 2ኛ እንዲሁም
▪️ምህረት አሻሞ ከ መከላከያ 14.28 ሶስተኛ ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሚካኤል ደጀኔ።
