ጅማ አባጅፋር ከሀዋሳ ከተማ 1ለ1 ተለያዩ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጅማ አባጅፋር ከሀዋሳ ከተማ የተገናኙበት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
በሊጉ አምስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ሁለተኛ ጨዋታ ጅማ አባጅፋር ከሀዋሳ ከተማ አንድ እኩል በወጡበት ጨዋታ የሀዋሳ ከተማው ምኞት ደበበ በ88ተኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ባስቆጠረው ጎል ጅማ አባጅፋርን ነጥብ እንዲያገኝ ቢያደርገውም የባከነ ሰአት ጭማሪ በሶስተኛው ደቂቃ ምኞት ደበበ ለሀዋሳ ከተማ ባስቆጠራት ጎል ነጥብ ተጋርተው ጨዋታው አልቋል።
ከጨዋታው በኋላ ጅማ አባጅፋር በሁለት ነጥብ እና በስምንት የጎል እዳ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አንድ ደረጃ ከፍ በማለት በ12ተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በአራት ነጥብ እና በአራት የጎል እዳ በ10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።