ኢትዮጵያ ቡና ሰበታ ከተማን 3ለ2 አሸነፈ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ሰበታ ከተማን 3ለ2 አሸንፏል፡፡
በመጀመሪያው አጋማሽ ሰበታ ከተማ በእስራኤል እሸቱ አማካኝነት መጀመሪያዋን ግብ በ13ኛው ደቂቃ ጎል ሲያስቆጥር፤ አቡበከር ናስር በ25ኛው ደቂቃ  ኢትዮጲያ ቡናን አቻ አድርጓል።
በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ ሀብታሙ ታደሰ  በ53ኛው ደቂቃ አቡበከር ናስር በ64ኛው ደቂቃ  ጎል በማስቆጠር ኢትዮጲያ ቡናን አሸናፊ አድርገውታል ። ለሰበታ ከተማዎች 2ኛዋን ግብ በቃልኪዳን ዘላለም በ76ኛው ደቂቃ  ግብ ማስቆጠር በመቻላቸው ጨዋታው 3ለ2 ተጠናቋል፡፡
 በቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጲያ ቡና እስካሁን በተደረጉት ጨዋታዎች 10 ነጥቦችን በመሰብሰን በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በአንደኝነት ሲቀመጥ ሰበታ ከተማ ደግሞ በአራት ነጥብ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.