ኢትዮጵያ ቡና ከአቶ ገዛሀኝ ጋር መለያየቱ ይፋ ሆነ!

ኢትዮጵያ ቡናን በሁለት ዙር ከ10 አመታት በላይ በስራ አስኪያጅነት የመሩት አቶ ገዛሀኝ ወልዴ ከክለቡ ጋር መለያየታቸው ታውቋል።

አቶ ገዛሀኝ ስራቸውን ለመልቀቅ ለቦርዱ ያስገቡት መልቀቂያ ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ በስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይተዋል።

አቶ ገዛሀኝ ወልዴ ከደጋፊዎች ቅሬታ ሲነሳባቸው እንደንነበር የምናስታውስ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በዘንድሮው የሲቢኢ ፕሪምየር ሊግ ካደረጋቸው 4 ጨዋታዎች በሁለቱ ሲሸነፍ፣ በአንዱ አቻ ወጥቶ፣ አንድ ደግሞ አሸንፏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.