የትራኳ ንግስት የምትሮጥበት የኒውዮርክ ማራቶን ነገ ይደረጋል!

በየአመቱ በጉጉት የሚጠበቀው እና በበርካታ ሺዎች የሚቆጠር ተሳታፊ የሚሮጥበት የኒውዮርክ ማራቶን ነገ ሲደረግ እንደሁልጊዜው ተጠባቂ አትሌቶችን ያሳትፋል።

የ2023ን የኒውዮርክ ማራቶን በወንዶች ባለድል የነበረው የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ ታምራት ቶላ ሲሆን በሴቶች ደግሞ ኬንያዊቷ ሄለን ኦብሪ ነበረች። እነዚህ ሀለት ባለድሎች ዘንድሮም ድላቸውን ለማስጠበቅ ይፋለማሉ።

በወንዶቹ ከታምራት ቶላ ጋር ይፎካከራል ተብሎ የሚጠበቀው  በኦሎምፒክ የታምራት ቶላ ተፎካካሪ ሆኖ የብር ሜዳሊያ ለሀገረ ቤልጅየም ያስገኘውና የአውሮፓ ፈጣን ሰአት ባለቤቱ ባሽር አብዲ ነው።

በሴቶቹ ሄለን ኦብሪ ሰትጠበቅ በ2022 የቦስተን እና የኒውዮርክ ማራቶንን ያሸነፈችበትን ታሪክ ለመድገም ትፋለማለች። በዚሁ አመት የቦስተን ማራቶንን ማሸነፏ ይታወሳል። በብዛት ከደረጃ የማትታጣው የሀገሯ ልጅ ሻሮን ሎኬዲም በውድድሩ ላይ አለች።

የ41 አመቷም ቪቪያን ቼርየትም ተሳታፊ ነች። ከዚህ በተጨማሪም የ3 ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ጥሩነሽ ዲባባ የመጀመሪያ የኒውዮርክ ማራቶኗን ትሮጣለች።

ውድድሩ እንደተለመደው አለም አቀፍ የቀጥታ ስርጭት የሚያገኝ ሲሆን በ’ Staten Island’ ጅማሮውን አድርጎ በ’ Centeral Park’ ይጠናቀቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.