ሊቨርፑል ተጫዋች ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል
አሰልጣኝ የርገን ክሎፕን አሰናብቶ አሰልጣን አርኔ ስሎትን የቀጠሩት ሊቨርፑሎች ስፔናዊውን የሪያል ሶሴዳድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ዙቢሜንዲ ለማስፈረም እንቅስቃሴ ሊጀምሩ መሆኑ እየተዘገበ ይገኛል ።
አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በዚህ ዓመት ከማንኛውም ነገር በላይ የመሐል ሜዳ ክፍላቸውን ማጠናከር እንደሚፈልጉ ይታወቃል ። በዚህም መሰረት ማርቲን ዙቢሜንዲን የመጀመሪያ አማራጫቸው መሆኑ ተገልጿል ።
ማርቲን 60 ሚልዮን ዩሮ ውል ማፍረሻ ሒሳብ እንዳለው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ሊቨርፑል ተጨዋቹ እና ክለቡን ለማነጋገር ማቀዱም ተዘግቧል።
ማርቲን ዙቢሜንዲን የማስመረሙ ፉክክር ውስጥ ማንቸስተር ዩናይትድም እንዳለበት ይታወቃል ።