አርሰናል እና ብሬንትፎርድ ነጥብ ተጋሩ
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከ ብሬንትፎርድ ጋር ነጥብ ሲጋራ ቶተንሀም በሌስተር ሲቲ አስደንጋጭ ሽንፈት አጋጥሞታል ።
የአርሰናልን ብቸኛ ግብ ትሮሳርድ ከመረብ ሲያሳርፍ የብሬንትፎርድን የአቻነት ግብ ደግሞ ኢቫን ቶኒ አስቆጥሯል።
በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርሰናል ሀምሳ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ 1ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ብሬንትፎርድ በሰላሳ አራት ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የሌስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ሜንዲ ፣ ማዲሰን ፣ ኢህናቾ እና ባርንስ ከመረብ ሲያሳርፉ የቶተንሀምን ብቸኛ ግብ ደግሞ ቤንታንኩር አስቆጥሯል።
ሌስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ በሀያ አራት ነጥብ አስራ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቶተንሀም በ ሰላሳ ዘጠኝ ነጥብ 5ኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላ የሊጉ መርሀግብር
ክሪስታል ፓላስ 1 – 1 ብራይተን
ፉልሃም 2 – 0 ኖቲንግሃም
ሳውዛምፕተን 1 – 2 ዎልቭስ