ቼልሲዎች አሁንም ነጥብ ጥለዋል!

ቼልሲዎች አሁንም ነጥብ ጥለዋል!

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር በለንደን ደርቢ ቼልሲ እና ፉልሀም ባደረጉት ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ለያይተዋል ።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ነጥቦችን በመሰብሰብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ፉልሀሞች በበኩላቸው ሰላሳ ሁለት ነጥቦች በመሰብሰብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።

በጨዋታው በቼልሲ በኩል አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ኢንዞ ፈርናዴዝ እና ሚካኤሎ ሙድሪክ በቋሚነት ጨዋታውን ሲጀምሩ ማዱኬ እና ፎፎና ደግሞ ከተቀያሪ ወንበር በመነሳት ተጫውተዋል ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቼልሲ ከ ዌስትሀም እንዲሁም ፉልሀም ከ ኖቲንግሀም ፎረስት የሚገናኙ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.