ማንቸስተር ሲቲ ድል አድርጓል ።

ማንችስተር ሲቲ ድል አድርጓል ።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከ ዎልቭስ ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ሶስት ግቦች ልማደኛው ኤርሊንግ ሀላንድ ከመረብ ሲያሳርፍ ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ ሀያ አምስተኛ የሊግ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም የሚጫወቱ ሲሆን ዎልቭስ ከ ሊቨርፑል የሚገናኙ ይሆናል ።

በሌላ መርሀ ግብር ሊድስ እና ብሬንትፎርድ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል ።

ሊድስ 0 – 0 ብሬንትፎርድ
ማንችስተር ሲቲ 3 – 0 ዎልቭስ
⚽️⚽️⚽️ሀላንድ 40′ 49′ 54′

Leave a Reply

Your email address will not be published.