ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ዲቻን አሸነፈ
ዛሬ 7:00 ሰዓት በተደረገ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ዲቻን 1 ለ 0 አሸነፈ።
ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን በ68ኛዉ ደቂቃ የተገኘዉን ፍፁም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር ሀድያ ሆሳዕና ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አስችሏል ።
በቀጣዩ 6ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ቅዳሜ ጥቅምት 26 9:00 ሰዓት ላይ ከመቻል የሚጫወት ሲሆን ሀድያ ሆሳዕና ከለገጣፎ ለገዳዲ ሰኞ ጥቅምት 28 12:00 ሰዓት ላይ ጨዋታዉን ያደርጋል።

