አርጀርቲና የ2022ቱን የኳታር አለም ዋንጫ ከፍ አደረገች ።
አርጀርቲና የ2022ቱን የኳታር አለም ዋንጫ ከፍ አደረገች ።
የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የ2018ቱን የሩሲያ ዓለም ዋንጫ አሸናፊ የሆኑትን ፈረንሳዮችን በመለያ ምት በመርታት አሸናፊ ሆነዋል ።
ለአርጀንቲናዊው የ7 ባሎንዶር ባለቤት ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ሆኖ ሲመዘገብ አርጀንቲናም በዓለም ዋንጫ ታሪኳ ሶስተኛውን የዓለም ዋንጫ ሆኖ ተመዝግቦላታል ።
ፈረንሳዊው ኮኮብ ኪሊያን ምባፔ በስምንት ጎሎች የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ኮኮብ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማ አሸናፊ ሲሆን ሊዮኔል ሜሲ የምሽቱ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጧል ።
የ2022ቱ የኳታር አለም ዋንጫ ምርጥ ወጣት ተጨዋች በመባል የ21 አመቱ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ ተመርጧል።
አርጀንቲናዊው የአስቶን ቪላ ግብ ጠባቂ ኤምሊያኖ ማርቲኔዝ የውድድሩ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመባል ወርቃማ ጓንት ተሸልሟል ።
ሊዮኔል ሜሲም የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች በመባል ከ2014ቱ የብራዚል አለም ዋንጫ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጧል።