ዛሬ በኦሪገን አትሌቶቻችን በ3 ውድድሮች ለወርቅ ሜዳሊያ ይፋለማሉ
በኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት ሶስት ተጠባቂ የፍፃሜ ውድድሮች ይደረጋሉ ።
በሴቶች ማራቶን ከቀኑ 10:15 ላይ ጎተይቶም ገ/ስላሴ ፣ አባበል የሻነህ እና አሸቴ በክሬ እንደ ወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያን በሜዳሊያ ለማንበሽበሽ የሚሮጡ አትሌቶች ናቸው ።
ውድድሩ ሊሊት 11:20 ሲቀጥል የወንዶች 3,000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል ።
ለሜቻ ግርማ ፣ ሀይለማርያም አማረ እና ጌትነት ዋለ ሀገራቸውን ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች እንደሆኑም ታውቋል ።
የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል እንደተጠናቀቀ የሴቶች 1,500 ሜትር ፍፃሜ ደግሞ ሲጀመር ሂሩት መሸሻ ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ እና ጉዳፍ ፀጋዬ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው ።