የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በሦስት ከተሞች በነገው ዕለት ጅማሮውን ያደርጋል።

የ2015 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በሦስት ከተሞች በነገው ዕለት ጅማሮውን ያደርጋል።
ውድድሩ በሦስት ምድቦች ተከፍሎ የአንደኛው ዙር ውድድር የምድብ ‘ሀ’ በባህር ዳር ፣ የምድብ ‘ለ’ በጅማ እንዲሁም የምድብ ‘ሐ’ በሆሳዕና የሚካሄድ ሲሆን ውድድሩ በሚካሄድባቸው ከተሞች የውድድሩ ኮሚቴ አባላት ከክለቦች ጋር የቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ተካሂዷል።
በቅድመ ስብሰባዎቹ የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ አባላት እና በከተማው የተወከሉ የፀጥታ ፣ የህክምና ፣ የሜዳ መስተንግዶ እና ተያያዥ ስራዎች የሚያከናውኑ የኮሚቴ አባላት ትውውቅ ከተደረገ በኋላ በዘንድሮ የውድድር አካሄድ ዙርያ በውድድር አዘጋጅ ኮሚቴዎች አማካኝነት ገለፃ ተደርጓል። ስኬታማ ውድድር ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከክለብ ተወካዮች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ከክለቦች የተነሱ ጥያቄዎችም በኮሚቴ አባላት ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

የአንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሚከተለውን ይመስላል፦👇

 

መረጃው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.