የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዝውውር ጊዜ አመቻቸ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትግራይ ክልል ባሉ ክለቦች ለመጫወት ውል ፈፅመው ለነበሩ ተጫዋቾች ልዩ የዝውውር ጊዜ አመቻቸ።
በትግራይ ክልል ባሉ ክለቦች ለመጫወት ውል ፈፅመው የነበሩ ተጫዋቾች በክልሉ በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ በመሆኑ የዝውውሩን ጊዜ ጠብቀው መዛወር አለመቻላቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ታህሳስ 22/2013ዓ.ም  በዚሁ አጀንዳ ላይ ባካሄደው ስብሰባ ለተጫዋቾቹ ልዩ የዝውውር ጊዜ ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን እንዳመነበት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።
በዚሁ መሰረት በትግራይ ክልል ክለቦች ይጫወቱ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ከታኅሣሥ 26 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ በማንኛውም ሊግ ውስጥ ተመዝግበው እንዲጫወቱ ፌዴሬሽኑ ፈቅዶላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.