የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን ለሚመሩ የጨዋታ አመራሮች የአካል ብቃት ፈተና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን ለሚመሩ የጨዋታ አመራሮች የአካል ብቃት ፈተና ተሰጠ

በ2015 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን ለሚመሩ የጨዋታ አመራሮች የአካል ብቃት ፈተና በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል።

በኢትዮጵያ ስፖርት አካካሚ በተካሄደው ፈተና ላይ 34 ዋና እና 56 ረዳት የጨዋታ አመራሮች ቀርበው 26 ዋና እና 52 ረዳት ዳኞች ማለፍ ሲችሉ 8 ዋና እና 4 ረዳት ዳኞች ፈተናውን ሳያልፉ ቀርተዋል።

ለጨዋታ አመራሮች የአካል ብቃት ምዘናው ከተከናወነ በኋላ አቶ ባህሩ ጥላሁን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ ፣ አቶ ሸረፋ ደሌቾ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ ፣ አቶ ከበደ ወርቁ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፣ አቶ ነብዩ ደምሴ የግዢና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፣ አቶ ሰለሞን እንዳለ የከፍተኛ ሊግ ም/ሰብሳቢ ፣ አቶ ሚኬሌ አርአያ የእግር ኳስ ዳኞችና ታዛቢዎች የሙያ ማህበር ም/ፕሬዚዳንት እንዲሁም የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ አባላት ከጨዋታ አመራሮችና ከጨዋታ ታዛቢዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

የእለቱ ውሎ ማሳረጊያ የነበረው ለጨዋታ አመራሮችና ታዛቢዎች በተሻሻሉ የእግር ኳስ ህጎች ዙርያ በተሰጠ ስልጠና ነው።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ጅማሮውን እንደሚያደርግ ይታወቃል።

ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በድረገጹ ዘግቧል

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.